የአእምሮ ዕድገት ውስንነት ተጋላጭነት

0
52

በእርግዝና ወቅት ከእናት ወደ ጽንስ የሚተላለፉ በሽታ አምጪ ተህዋሲያን የሕጻናቱን የአእምሮ ዕድገት ውስንነት የመጋለጥ ዕድል በሦስት እጥፍ እንደሚጨምሩ ሳይንስ ዴይሊ ድረ ገጽ ሰሞኑን ለንባብ አብቅቶታል፡፡

በሲዊዲን የካሮሊኒስካ የምርምር ተቋም  ለንባብ እንዳበቃው በሦስት ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ሰዎች ላይ በተካሄደ ጥናት እና ምርምር  በእርግዝና ወቅት “ሳይቶሜጋሎ ቫይረስ ፣ቶክስ ፕላዝማ እና “ኻርፐስ ቫይረስ”ን የመሳሰሉ ተህዋሲያን ወደ ጽንስ ሊተላለፉ እንደሚችሉ ተረጋግጧል፡፡ በተላላፊ በሽታ አምጪ ተህዋስያኑ የተያዙ ልጆች  ለአእምሮ ዕድገት ውስንነት የመጋለጥ ዕድላቸው በተህዋስያኑ ካልተያዙት ከሦስት እጥፍ በላይ ከፍ ያለ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

በእርግዝና ወቅት  የእጅ ንጽህናን በመጠበቅ እና ያልበሰለ ምግብ ከመመገብ በመቆጠብ ተጋላጭነትን መቀነስ እንደሚቻል ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የመስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here