የሊዝ የጨረታ ማስታወቂያ

0
26

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የሚደነግገውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8/1 መሰረት በ2019 በጀት አመት ለ1ኛ ዙር ጨረታ ለመኖሪያ ቤት ብዛት 9፣ ለድርጅት ብዛት 2 ለማኒፋክቸር ብዛት 1 በድምሩ 12 ቦታዎችን በጨረታ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው  ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 3 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) በመመሪያ ቁጥር 1/2005 አንቀጽ 21 ንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት የጠቅላላ የቦታው ስፋት መነሻ ዋጋው ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 25 በመቶ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 11፡30 ብቻ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 3 ማስገባት ይችላሉ፡፡
  3. ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን በ11፡30 ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው የሚከፈተው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን 3፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ካልሆነም ተወካዮችም ሆነ ግለሰቦቹ ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ በተመለከተ በነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 03 ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ይሆናል፡፡
  5. ይህ ማስታወቂያ ተግባራዊ የሚሆነው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆናል፡፡
  6. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በጽ/ቤቱ የማስታወቂያ ሰሌዳ ወይም በስልክ ቁጥር 058 445 14 74 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ሌሎች ተጨማሪ ዝርዝር ሃሳቦችን (ህጎችን) ከሚሸጠው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here