ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
48

የጭልጋ ወረዳ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ ቡድን መሪ በበጀት ዓመቱ  ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1. የእህል አቅርቦት፣ ሎት 2. የወጥ ማጣፈጫ፣ ሎት 3. የማገዶ እንጨት፣ ሎት 4. አትክልት፣ ሎት 5. የምግብ ዘይት እና ፊኖ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ከተቋሙ ድረስ የሚያቀርቡ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማሰረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) የሚያቀርቡ፡፡
  4. የግዥው መጠኑ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት  ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ለግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ የሚሞሉትን አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. የጨረታ አሸናፊ ድረጅት የአሸነፈውን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ  (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  9. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት የአሸነፈውን እቃ ጭልጋ ማረ/ቤት መጋዘን ድረስ የሚያቀርብ መሆኑን አለበት፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ቅጅዎች ማለትም ዋናውንና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጭልጋ ወረዳ ማ/ቤት አስ/ጽ/ቤት ግዥ /ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በተከታታይ ቀናት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከጥቅምት 02/2019 እስከ ጥቅምት 13/2019 ዓ.ም 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው ሳጥን ጥቅምት 16/2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ላይ ይታሸጋል፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ ቡድን መሪ ጥቅምት 16/2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃና ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 333 22 02 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  • ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፡፡
  • በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች በጥቅል ዋጋቸው አሸናፊው ይለያል፡፡

 የጭልጋ ወረዳ ማረሚያ ቤት አስ/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here