የጎንደር አካል ጉዳተኞች ክ/ማ/ማዕከል የ2019 ዓ/ም በመደበኛ በጀት አመት አላቂ ዕቃዎች እና ቋሚ ዕቃዎችን ማለትም፡- ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3. ብረታ-ብረት ዕቃዎች፣ ሎት 4. MDFና ጣዉላ፣ ሎት 5. ኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ ሎት 6. የሞባይል አክሰሰሪዎች፣ ሎት 7. ጨርቃ-ጨርቅ፣ የሱፍ ክር፣ የመኪና ክርና አክሰሰሪዎች፣ ሎት 8. የህክምና መድሃኒቶች፣ ሎት 9. ራቨርቲፕስና ሀንድል፣ ሎት 10. የዊልቸር መለዋወጫ ዕቃዎች፣ ሎት 11. ሸቀጣሸቀጥ ዕቃዎች፣ ሎት 12. የፕላስቲክ ዕቃዎች፣ ሎት 13. የህትመት ቀለሞች፣ ሎት 14. የመኪና ጎማ፣ ሎት 15. የእንጨትና የብረታ-ብረት ማሽኖች ጥገና፣ ሎት 16. ሽመናና ስጋጃ መሳሪያዎች፣ ሎት 17. ኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣ ሎት 18. የልብስ ስፌት ጥገና፣ ሎት 19. የሹራቭ ማሽንኖች፣ ሎት 20. ኤሌክትሮኒክስ ጥገና እንዲሁም ሎት 21. ለሰልጣኞች የምግብ አቅርቦት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተለውን ማሟላት አለባቸው፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በታች ለሆኑ ግዥዎች ያለ ቫት መወዳዳር ይችላሉ፡፡
- የጨረታዉ አሸናፊ የሚለየው በሎት ድምር ያቀረበ ተጫራች ነዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የዋጋውን አንድ በመቶ በዋስትና ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ማዘዣ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የምግብ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አንድ በመቶ የባንክ ማዘዣ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ግዥና/ፋ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማዘጋጀት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ዘወትር በተከታታይ ቀናት ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ማለትም ጥቅምት 02/2019 እስከ ጥቅምት 16/2019 ይቆይና የመክፈቻ ቀኑም በ16ኛው ቀን ጥቅምት 16/2019 ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በማዕከሉ ግዥ/ፋ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ሰዉ ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
- ሙሉ መግለጫዉን /ዝርዝር/ እና መመሪያዉን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በማዕከሉ በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 211 72 33 /09 18 62 30 87 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻችን ጎንደር ከተማ ቂርቆስ ቀበሌ 06 አሽዋ ሜዳ ት/ቤት/ጎን ነው፡፡
ማሳሰቢያ;- መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የጎንደር አካል ጉዳተኞች ክ/ማ/ማዕከል

