ጊዜያዊ የረዥም ጊዜ ኮንትራት ቅጥር  ማስታወቂያ

0
9

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን  ከዚህ በታች ያሉትን   ክፍት የስራ መደቦች ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታውን ከሚያሟሉ  ስራ ፈላጊዎች መካከል በጊዜአዊ የረዥም ጊዜ /በኮንትራት /ቅጥር አወዳድሮ በመቅጠር ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ተቁ የሥራ መደቡ መጠሪያ ደረጃ የመ/መ/ቁ ደመወዝ ብዛት ዳይሬክቶሬት የሥራ ቦታ አግባብ ያለው የትምህርት ዝግጅት አግባብ ያለው የስራ ልምድ
1 ስርጭት ተቆጣጣሪ /ሱፐር ቫይዘር1/ 13 አሚ-1608 በኮርፖሬሽኑ የደመወዝ ስኬል መሰረት 01 አዲስ አበባ ሚዲያ ቴክኖሎጂ አዲስ አበባ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮምፒውተርና ኤሌክትሮ ሜካኒካል፣ በብሮድካት ምህንድስና እንዲሁም በመረጃና ኮምንኬሽን ቴክኖሎጂ፣ በኤሌክትሮኒክስና ተግባቦት ቴክኖሎጂ፣ መልቲሚዲያና ኤሌክትሮኒክስ ኢኪውፕመንት ሰርቪሲን፣ በኤሌክተሮኒክስና ተግባቦት ቴክኖሎጂ ስራ አመራር ወይም ተዛማጅ የትምህርት መስክ የሰለጠነ የመጀመሪያ ዲግሪና 5 ዓመት ወይም 2ኛ ዲግሪና 3 ዓመት አግባብነት ያለው የስራ ልምድ

 

ማሳሰቢያ፡-

  • የምዝገባ ቀን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን  ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል፡፡
  • አመልካቾች ለፈተና በሚቀርቡበት ጊዜ ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • አመልካቾች በእምነት ማጉደል በማጭበርበር ወይም በስርቆት ወንጀል ተከሰዉ ስልጣን ባለዉ አካል ተፈርዶባቸዉ የመቀጠር መብታቸዉን እንዲጠቀሙ ስልጣን ያለዉ ፍርድ ቤት የወሰነበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • አመልካቾች ለፈተና በሚቀርቡበት ጊዜ ኦርጅናሉን የትምህርትና የስራ ልምድ ለተጠየቀበት መደብ ብቻ የስራ ልምዳቸውን መረጃ ኦርጅናል ይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  • ከተጠቀሰዉ አግባብነት ያለው የትምህርት ዝግጅት እና የስራ ልምድ ውጭ ለምዝገባ የሚቀርቡ ሌሎች ማስረጃዎች ተቀባይነት አይኖራቸዉም፡፡
  • አመልካቾች መልካም ስነ-ምግባር ያለው/ላት፡ ከማንኛውም ደባል ሱስ የፀዳ/ች፣ ጥሩ ስብዕና ያለው/ላት፡፡
  • ተወዳዳሪዎች በተመዘገቡበት የስራ መደብ ለምን ተቀጥረው መስራት እንደፈለጉ በጽሁፍ ገልፀው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • አመልካቾች የሙያ ብቃት በሚያስፈልጋቸው የት/ት ዝግጅት የብቃት ማረጋገጫ በማስታወቂያው በተጠየቀው የት/ት ደረጃ ልክ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • የሙያ ብቃት ምዘና ያልተጀመረባቸው የትምህርት መስኮች ከሚመለከተው ተቋም የሙያ ብቃት አለመጀመሩን ማስረጃ ካቀረቡ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
  • የኮንትራት ቅጥሩ ለ6 ወር ሆኖ እንደአስፈላጊነቱ በየ6 ወሩ ይታደሳል፡፡
  • ተወዳድሮ ያለፈ የስራ ተያዥ/ዋስ/ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  • ፈተና የሚሰጥበት ቀንና ቦታ በሌላ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡
  • አመልካቾች የምትመዘገቡበት ሊንክ በዌብሳይታችን ameco.et ማግኘት ትችላላችሁ ወይም

ይህ ሊንክ በመጫን ይመዝገቡ https://forms.gle/JpBsz2cQuii2oiS69   መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

  • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 226 50 07 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

ባህር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here