በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ በምዕ/ጐጃም ዞን ገንዘብ መመሪያ የደም/ዙ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳዉ ዉስጥ በሚገኙ ባለበጀት መ/ቤቶች ያሉ ሎት l. ቁርጥራጭ ብረታብረቶች፤ አገልግሎት የሰጡ የመኪና መለዋወጫወች እና የአገለገሉ የተለያዩ የቢሮ ፕላንትና ማሽነሪ እና የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፤
- ሎት l. ቁርጥራጭ ብረታብረቶችና የተሸከርካሪ መለዋወጫ ለሚሳተፉ፤
- በዘርፉ የተሰማሩ እና በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ አና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ያገለገሉ ንብረቶችን መግዛት የሚፈልጉ ግን ንግድ ፈቃድ ያለዉም ይሁን የሌለው ድርጅትና ግለሰብ መጫረት ይችላል፡፡
- በሽያጭ የሚወገዱ ቁርጥራጭ ብረቶችና ንብረቶችን መግዛት ወይም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ የንብረት ሽያጭ የጨረታ ሰነዱን ደም/ዙ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በመቅረብ 1ዐዐ (አንድ መቶ) ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው በበኩር ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15/አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀን በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡ዐዐ ታሽጐ 4፡ዐዐ ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- በተራ ቁጥር 4 የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ስዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በንብረት ሽያጭ ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በሲፒኦ ወይም ደም/ዙ/ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በደረሰኝ በማስያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በንብረት ሽያጭ ጨረታ የሚሳተፍ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ ስም፣ ፊርማ እና አድራሻ በማስቀመጥ ደም/ዙ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ስዓት የጫራታ ሳጥኑ እስከሚዘጋበት ቀንና ስዓት ድረስ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ የንበረት ሽያጭ ጫራታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በንብረት ሽያጭ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደም/ዙ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር ዐ58773ዐ274 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ደምበጫ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

