የጃዊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግ/ፋ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. ፈርኒቸር የአገር ውስጥ ሎት 2. ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድር መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ኮፒውን በፖስታ በማሸግ በሁሉም ሰነዶች ላይ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ሙሉ አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር በማስፈር ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ሙሉ በሙሉ ዋጋቸውን ያልሞላ ተጫራቹ ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት የሚለየው በጠቅላላ ድምር ውጤት ነው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጲያ ብሄራዊ ባንክ በተመሰከረለት (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ የዋጋውን አንድ በመቶ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምር ከሰኔ 1/2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 15/2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት ድረስ የጨረታ ሰነዱን ከጃዊ የመጀ/ደ//ግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኔ 16/2018 ዓ/ም በ4:00 ታሽጎ 4:30 ይከፈታል፡፡
- ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝሩን (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ያገኙታል፡፡
- እቃውን ጃዊ የመ/ደ/ሆ መካዝን ድረስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተቋሙ የጨረታውን ከጠቅላላ ድምሩ 20 በመቶ የመቀነስና የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 278 03 05 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የጃዊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

