አቢያታ ሻላ ሐይቅ ብሔራዊ ፓርክ

0
5

የአቢያታ ሻላ ሐይቅ ብሔራዊ ፓርክ በኦሮሚያ ክልል ነው የሚገኘው፡፡ ፓርኩ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ 200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተከለለ ሲሆን ስፋቱም 887 ኪሎ ሜትር ስኩዌር ተለክቷል፡፡ ከተጠቀሰው ስፋቱ ውስጥ አቢያታ እና ሻለ ኃይቆች 443 ነጥብ አምስ ኪሎ ሜትር ስኩዌሩን ይዘዋል፡፡የፓርኩ መገኛ ከዝቅተኛው 1540 ሜትር እስከ ከፍተኛው 2075 ሜትር ተለከቷል፡፡ በፓርኩ ቀጣና ውስጥ የሚገኙትን አቢያታ እና ሻላ ሀይቆችን በመካከላቸው የሚገኝ ሦስት ኪሎ ሜትር አግድም የተለካ ኮረብታ ይለያያቸዋል፡፡በፓርኩ ከ300 በላይ የዓእዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ፡፡ ከነዚህ ውስጥ “ፍላሚንጐ” የተሰኙ የዓእዋፍ ዝርያ ከፍተኛውን ቁጥር ይዘዋል፡፡

በተጨማሪም “ኃይትፔሊካን” የተሰኙቱ በብዛታቸው በተካታይነት ሰፍረዋል- በድረገፆች፡፡ፓርኩ  ከኃይቆቹ በተጨማሪ ሳር ለበስ ሜዳን ያካተተ ሲሆን በፓርክነት ለመመሰረቱ ዋነኛው ምክንያት ዐእዋፉን ለመጠበቅ መሆኑን ነው ድረገፆች ያስነበቡት፡፡ በፓርኩ ከዱር እንስሳት የሜዳ ፍየል፣ ዝንጀሮ፣ ቀበሮ እና ጅብ መገኘታቸው ተረጋግጧል፡፡ ልዩ ቀጣና ተከልሎ ጥበቃ የሚደረግለት የሰጐን ማርቢያም ተጠቃሽ ነው -በፓርኩ፡፡ለፓርኩ ዘላቂነት ወይም ጠብቆ ለማቆየት በዙሪያው የኗሪዎች መስፈር እና ለእርሻ መሬት የፓርኩን ክልል መግፋት፣ ለማገዶ እና ከሰል ምርት የግራር ደንን መጨፍጨፍ በስጋትነት ተቀምጠዋል፡፡ለዘገባችን በመረጃ ምንጭነት ብሪሊያንት ኢትዮጵያ፣ ቪዚት ኢትዮጵያ እና ዊኪፒዲያን ተጠቅመናል፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሰኔ 8  ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here