በማእከላዊ ጎንደር ዞን የምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አማካኝነት ለምሥራቅ ደንቢያ ወረዳ አስተዳደር ቢሮ ግንባታ 3ተኛ ዙር የጣራ፣ ዲች እና ሴፊቲ ታንከር ሥራዎች የእጅ ዋጋ ግንባታ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸውና ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከደረጃ ስድስት እና ከዚያ በላይ የሆኑ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከሰኔ 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ በምሥራቅ ደንቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የግንባታ ዝርዘር መገለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 ከሰኔ 15/2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 05/2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩት ጠቅላላዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረስኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በታሸገ ፖስታ በምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በ22 ቀን ሐምሌ 06/2018 ዓ.ም በ3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጣራ ስራና ሌሎች ሥራዎችን ሐምሌ 6/2018 ዓ.ም በ22ኛው ቀን 3፡30 ተዘግቶ በምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 በዚሁ ቀን በ4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ለጨረታው መሟላት የሚገባቸው ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች በሌሉበት ጽ/ቤቱ የጨረታውን ፖስታ የመክፈት ስልጣን አለው፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቹ (ተወዳዳሪው) አሸናፊነቱ ተገልፆለት ውል ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ ያሸነፊውን 3ኛ ዙር የጣራ ስራና ሌሎች ሥራዎችን ሥራ መጀመር ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቹ የሞላው ጠቅላላ ዋጋ ከማሀንዲስ ግምቱ 10 በመቶ በላይ ከሆነ እና ከ25 በመቶ በታች ከሆነ ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 335 06 01 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- ከዚህ በፊት በየትኛዉም ደረጃ በነበራቸዉ የአፈጻጸም ችግር ምክንያት የታገዱ ተጫራቾችን አይመለከትም፡፡
የምስራቅ ደንቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

