የነገ ተስፋ የተቀናጀ የልማት በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ጽ/ቤቱ ጎንደር ከተማ ቀበሌ 13 የሚገኘው 2018፣ 2019 እና 2020 የ3 ተከታታይ የበጀት ዓመት ሂሳቡን ኦዲት የሚያደርግለት የውጭ ኦዲተር በጨረታ አወዳድሮ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል፡፡
- የ2018 ዓ.ም የታደሰ የሙያ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የ2018 ዓ.ም ታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከዚህ በፊት ለንግድ ያልተቋቋሙ ድርጅቶችን (CSO/NGO) ኦዲት ያደረገባቸውን ቢያንስ 3 (ሶስት) መልካም ሥራ አፈጻጸም ልምድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ለተከታታይ 3 (ሶስት) ዓመታት፣ ማለትም ለ2018፣ 2019 እና 2020 በጀት ዓመታት የድርጅቱን ሂሳብ ኦዲት ለማድረግ ፈቃደኛ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች ለአገልግሎት የሚጠይቁትን የአንድ ዓመት የኦዲት ዋጋ ታክስ በመጨመር ማስገባት አለባቸው፡፡ እንዲሁም የሚያቀርቧቸው የቴክኒክ ሠነድ እና የዋጋ ሠነድ በተለያዩ ፖስታዎች ታሽገው መሆን አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከድርጅቱ ቀርበው የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 (ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሠነዱን ጎንደር ከተማ ቀበሌ 13 ካሰኝ ዓለማየሁ ሆቴል ፊት ለፊት ከሚገኘው ግርማ ህንፃ የድርጅቱ ቢሮ መግዛት እና ሠነዱን ሞልተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ጨረታው ይዘጋል፡፡
- ጨረታው የሚመለከታቸው የድርጅቱ ሠራተኞች እና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት በድርጅቱ ቢሮ ጨረታው በተዘጋበት በማግስቱ ከረፋዱ 4፡00 ላይ በይፋ የሚከፈትና ውጤቱ በግልጽ የሚታወቅ ይሆናል፡፡
- ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 111 01 34 /09 18 77 47 45 ደውለው ተጨማሪ መረጃና ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የነገ ተስፋ የተቀናጀ የልማት በጎ አድራጎት ድርጅት

