የነዳጅ ፍጆታን ለመቀነስ የታሰበው

0
21

በሩሲያ አሽከርካሪዎች -የተሽከርካሪ የነዳጅ ፍጆታን ለመቀነስ ያስችላል የተባለ “ኦይል ታብሌት” የነዳጅ እንክብልን እየተጠቀሙ መሆኑን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ ከሰሞኑ ለንባብ አብቅቶታል፡፡

ሩሲያ እና ዩክሬን በማካሄድ ላይ ባሉት ጦርነት ዩክሬን በሩሲያ የነዳጅ ክምችት ላይ በሰነዘረችው ጥቃት እና ባደረሰው ውድመት የነዳጅ ዋጋ  ጣሪያ ነክቷል፤ እጥረትም ተከስቷል- ድረ ገጹ እንዳስነበበው፡፡ ለዚህ ችግር የተዳረጉ የሩሲያ ዜጐችም ከፊሉ ተሽከርካሪን ማቆም፣ ቀሪዎቹ ደግሞ የተለያየ መፍትሄ ያሉትን መከወን ላይ ደርሰዋል፡፡ ከነዚህም መካከል ታዲያ “ታምራዊ እነክብል” የተሰኘን የከወኑቱ ለየት ብለው ሽፋን አግኝተዋል፡፡

በነዳጅ እጥረት እና ውድነት ከተነኩት መካከል ከፊሎቹ የ“ሜራክል ፒልስ” ተዓምራዊ የነዳጅ እንክብልን ተግባራዊ እያደረጉ ነው- ባዝ የተሰኘ የቴሌግራም የዜና ምንጭን ጠቅሶ ድረ ገጹ እንዳስነበበው፡፡ ቀደም ባሉት ጊዜያት የነዳጅ እንክብሎቹ  ሲሸጡ ከነበሩበት ዋጋ ከሁለት እጥፍ በላይ ጨምረዋል፡፡

የነዳጅ  እንክብሎቹ “ቡቃ” እና “ቢኢኮ” በተሰኘ መጠሪያ ወይም “ብራንድ” የነዳጅ ቃጠሎን ያረጋጋል፣ ውስጣዊ የሞተሮች ፍጥነትን ያሳልጣል፣ በጥቅሉ የነዳጅ ፍጆታን ይቀንሳሉ በሚልም አገልግሎት ላይ እንደሚውሉ ነው የተጠቆመው፡፡

የነዳጅ እንክብሎቹ በነዳጅ ማደያዎች አንዱ እስከ አንድ ዶላር ሊገዙ እንደሚችል ያስነበበው የድረ ገጹ ጽሁፍ አንድን እንክብል ለ200 ሊትር ቤንዚን እንደሚያውሉትም  ከተጠቀሚዎች የተገኘን መረጃ አስፍሯል -ድረ ገጹ፡፡

በመጨረሻም እንክብሎቹ እንዴት እንደሚሰሩ በውል አለመታወቁን የጠቀሱት ባለሙያዎቹ በነዳጅ ውስጥ ካለው ጋር ሲገናኝ የነዳጅ መርጫ መርፌ ወይም የሞተር ችግር ሊያስከትል ይችላል ሲሉ ነው ያስጠነቀቁት፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሰኔ 29   ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here