ሐራጅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
11

የመተማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ሥር የሚገኙ የወዳደቁ አገልግሎት ጊዜያቸውን የጨረሱ የከባድ ማሽነሪ እቃዎች፣ የእስካቫተር መለዋወጫ እቃዎች፣ የዶዘር መለዋወጫ እቃዎች፣ የትራክተር ቦዲ፣ ርሎ መዳመጫ፣ ኢነትሪ መኪና መለዋጫ እቃዎች እና ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን በሐራጅ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2. ግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. በጨረታው ያገለገሉ እቃዎች ቁራልዮ (scrape) ጅምላ፣ በቆራሊዮ ፈቃድ ያላቸው፤ በብረታ ብረት ማቅለጥ ድርጅት ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 5 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) በባንክ ወይም በኢትዮጲያ ብሔራዊ ባንከ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንት ማቅረብ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከመ/ቤቱ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ አብረው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች በተገለፀው ዕቃ አይነት በጥቅል መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ንብረቱን በመቸርቸር (በነጠላ መረከብ) መወዳደር አይችሉም፡፡ ስለ ንብረቶቹ አይነትና ብዛት በጨረታ ሰነድ ላይ ያገኙታል፡፡ በተጨማሪ መተማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ማየት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለያንዳነዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር (30) መግዛት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ይቆያል በ16ኛው ቀን ይከፈታል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸጉ ፖስታዎች በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን 4፡30 ታሽጎ 5፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግልጽ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን በመተማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር (30) መውሰድ ይችላሉ፡፡
  10. በተሰጠው የጊዜ ገደብ ያሽነፈበትን ገንዘብ በ10 ቀናት ውስጥ በመ/ቤቱ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡ ገቢ ካላደረጉና ዕቃዎችን ካልተረከቡ ዋስትና ያስዘው ገንዘብም ሆነ ለዕቃው የከፈለው ዋጋ ለመንግስት ገቢ ሆኖ ዕቃዎቹ በድጋሜ ሽያጭ ይውላሉ፡፡
  11. አሽናፊዎች እቃውን የሚረከቡት በመተማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 30 ድረስ በመምጣት እና አስረካቢዎችን በማግኘት ይሆናል፡፡
  12. የሐራጅ ጨረታ አሽናፊው ድርጅት የጨረታው አሽናፊነት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በወረዳው ዐቃቢ ህግ ጽ/ቤት በመቅረብ ውል መውሰድ አለበት፡፡
  13. ተጫራቾች የሚጫረቷቸውን ዕቃዎች ናሙናዎችን ዕቃዎቹ በሚገኙበት ማለትም በመተማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በአካል ቀርበው ማየት ይችላሉ፡፡
  14. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በትክክል ሥርዝ ድልዝ ሳይኖርበት መሙላትና በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የተወዳዳረው ስም፣ አድራሻ፣ ፊርማ እንዲሁም የሚወዳደሩበት የንብረት አይነት ስም በመጥቀስ በፖስታው ላይ መግለጽ ይኖርበታል፡፡ አንድ ተጫራች በሁሉም የሽያጭ ንብረት ሊወዳደር ይችላል፡፡
  15. መ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 331 00 47 በመደወል ወይም ቢሮ ቁጥር 30 በአካል በመምጣት ማግኘት ይችላሉ፡፡

የመተማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here