ምርምር – ለአእምሮ ጤና

0
35

በእንቅልፍ ወቅት በራስ ቅል እና በአንጐል እንዲሁም በጥልቅ አንጐል ውስጥ ቆሻሻን ማፅዳት የሚያስችል የፈሳሽ ዝውውር መኖሩ በሰው ሰራሽ አስተውሎት “ኤ አይ” መረጋገጡ ለአልዛይመር የመርሳት በሽታ እና ሌሎች በአንጐል ላይ ለሚደርሱ  ጉዳቶች መድኃኒት ለመሻት በር ከፋች መሆኑን ሳይንስ ዴይሊ ድረ ገጽ ሰሞኑን ለንባብ አብቅቶታል፡፡

 

በአሜሪካ የሮችስተር ዩኒቨርሲቲ በመረጃ ምንጭነት እንዳስነበበው ተመራማሪዎች በሰው ሰራሽ አስተውሎት በአንጐል ውስጥ የፈሳሽ ዝውውር መኖሩን እና የዝውውሩ ፍጥነት በጥልቅ አንጐል ህዋሳት ውስጥ ከአንጐል ውጪ ከሚገኘው 50 እጥፍ  እንደሚቀንስ መገንዘብ ችለዋል፡፡ ግኝቱም ለአልዛይመር በሽታ፣ የአንጐል መወጠር ወይም  መጨናነቅ ለመሳሰሉት መድኃኒት ለመሻት እንደሚረዳ ነው ያሰመሩበት፡፡

 

በጥናቱ ውስጥ የተሳተፉ ተመራማሪዎች    ‘ግኝቱን በውል ለመከታተል ከ ኤም አር አይ’ የተሻለ ነው ብለው ባመኑበት በ “ኤ አይ” የፈሳሽ ዝውውር ፍጥነቱን ለማስላት ተገልግለውበታል፡፡

በዚህም የደም ስር ማስተላለፊያዎች ከአንጐል የሚወጡ ቅንጣቶች የሚወገዱባቸው ከመርሳት በሽታ ጋር የተያያዙ “አሚሎድ ቤታ” የተሰኙ ፕሮቲንን ጨምሮ… የመጓጓዝ ፍጥነታቸው የተለያየ መሆኑም ተገንዝበዋል፡፡

 

የተመራማሪዎች ቡድን በአንጐል ውስጥ የፈሳሽ ዝውውርን ለመወሰን አይጥን በመሳሰሉ መሞከሪያ እንስሳት ላይ ተመስርቶ የመነሻ መለኪያዎችን ለመወሰን የ “ኤ አይ” መለኪያ መሣሪያን ውጤታማነት ለማሳደግ በመስራት ላይ መሆኑ ነው የተብራራው፡፡፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የነሐሴ  18  ቀን 2018 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here