የነፋስ ግፊትን የረታው አሽከርካሪ

0
24

እንግሊዛዊው አንዲ ግሪን  ሁለት ሀይድሮጂንን በኃይል ምንጭነት የሚገለገሉ ሞተሮች በተገጠሙለት 1 ሺህ 600 የፈረስ ጉልበት ባለው ተሽከርካሪ 653 ነጥብ 908 ኪሎ ሜትር በሰዓት በማሽከርከር ክብረ ወሰን ማስመዝገቡን ዘጋርድያን ድረ ገጽ ሰሞኑን ለንባብ አብቅቶታል፡፡

 

ዓለም አቀፍ የሞተር ስፖርት አስተዳደር አካል የሆነውን “ፌሬሽን ኢንተርናሽናል ዴላ አውቶሞቢል” ን በመረጃ ምንጭነት የጠቀሰው ድረ ገጹ የ64 ዓመቱ አንዲ ግሪን በአሜሪካ ዩታ ግዛት በእንግሊዝ የግንባታ መሳሪያ አምራች ኩባንያ “ጄሲቢ” በተሰራ ዘጠኝ ነጥብ አምስት ሜትር በሚረዝም ኦክስጂንን የሀይል ምንጭ ባደረገ ተሽከርካሪ ለክብረ ወሰን መብቃቱን ይፋ አድርጓል፡፡

 

አንዲ ግሪን በ2006 ናፍጣን በሀይል ምንጭነት በሚጠቀም ተሽከርካሪ 563 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር በሰዓት በመፈትለክ በቦኒቪል ሜዳ ክብረ ወሰን ማስመዝገቡ ተጠቅሷል፡፡ ባለፈው ማክሰኞ እለትም “የወደፊቱ የኃይል ምንጭ” በሚል በሰየመው ኦክስጂንን በሀይል ምንጭነት በሚገለገል ተሽከርካሪ ቀደም በሎ በአንዲ ግሪን የተያዘውን 298 ኪሎ ሜትር በሰዓት በ168 ኪሎ ሜትር በመብለጥ ነው ክብረ ወሰን መስበር የቻለው፡፡

 

የአንዲ ግሪን ክብረ ወሰን ከድምፅ ከሚፈጥነው  “ሱፐር ሶኒክ” ፍጥነት ጋር ባይቀራረብም የተሽከርካሪ አምራች ኩባንያው መሀንዲሶች ከብክለት የፀዳ የሀይል ምንጭ የሆነውን ኦክስጂንን ወደፊት የሚያሻግር ርምጃ መሆኑ ታውቋል፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር  የነሐሴ  18 ቀን 2018 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here