የሠላሳ ሁለት ዓመቷ ጃፓናዊት የተለያዩ የሂሳብ ቁጥሮችን ተጠቅማ ሹኢሻ ከተሰኘ የ “ኦንላይን” መደብር ሁለት ሺህ የግዢ ትአዛዝ ሰጥታ ሲደርሷት ባለመቀበል እና ግዢውን በመሰረዝ በድርጅቱ ላይ ላደረሰችው ኪሳራ ተጠያቂ መሆኗን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ ከሰሞኑ አስነብቧል፡፡
በጃፓን ካሉ ትልልቅ አሳታሚዎች አንዱ በሆነው “ማንጋ ኢንክ” በኦንላይን” በቀጥታ የስልክ ትእዛዝ በሺህ የሚለኩ የግዢ ትእዛዞችን በመስጠቷ ሻጩ ድርጅት ቁሶቹን በቦታው ሲያደርስ ተረካቢዋ ወይም አዛዧ ትእዛዟን በመሰረዝ ለኪሳራ ዳርጋለች ነው የተባለው፡፡
በ2024 እና 2025 ሃያ ሰባት ነጥብ ሁለት ሚሊዬን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን በማዘዝ እና ባለመክፈል ለኪሳራ ማብቃቷ ነው በድረ ገጹ የተብራራው፡፡
ድርጅቱም ግለሰቧ የንግድ ስራዉን አስተጓጉላ በአጠቃላይ የ47 ሚሊዬን ዶላር ኪሳራ ያደረሰችበት መሆኑን በመግለጽ ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ አስተማሪ ርምጃ እንዲወሰድባት ጠይቋል፡፡
ፖሊስም ለአንድ ዓመት ባደረገው ክትትል ግለሰቧን አግኝቶ ለቀረበባት ክስ በሰጠችው መልስ በእለት ተእለት ሕይወቷ የደረሰባትን ጭንቀት ለመቋቋም ብቸኛ መፍትሄ አድርጋ ደርጊቱን መፈፀሟን አምናለች፡፡
(ታምራት ሲሳይ)
በኲር የነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም


