የአገው ግምጃ ቤት ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በድርጅቱ የውሃ መገኛ ቦታ ላይ የሚገኘውን ጀኔረተር በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
- ጨረታው ለማንኛውም ተጫራች ክፍት ነው፡፡
- የዋጋ ዝርዝር መግለጫ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩት ከጠቅላላ ዋጋ የማመለስ 5 በመቶ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለበቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በድርጅታችን ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በጨረታ ፖስታ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የመጫረቻ ሰነዱን አገው ግምጃ ቤት ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግቢ ግዥና ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ከፍለው መግዛት ይችላሉ፡፡
- የመጫረቻ መነሻ ዋጋ ብር 2,000,000 (ሁለት ሚሊዮን ብር) ሲሆን ዝርዝር መግለጫው በሰነዱ ላይ ያለ በመሆኑ መጫረት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከነሐሴ 18/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ ጳጉሜ 2/2018 ዓ.ም 11፡00 ድረስ በሥራ ሰዓት ቅዳሜን ጨምር ሰነዱን መግዛት የምትችሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ህዝባዊ በዓል ከሆነ በቀጣዩ ቀን 8፡00 ታሽጎ 8፡15 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቻው በተገኙበትና ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ሙሉ ክፍያውን ዕቃ እስካለበት ቦታ ድረስ ዕቃውን መረከብ እና ክፍያ በባንክ ገቢ የተደረገውን ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ቀን ክፍያ ባይፈጽሙ የጨረታ ማስከበሪያ ለድጅቱ ገቢ ሆኖ ድርጅቱ ሌላ አማራጭ የሚጠቀም መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊ የሚለይበት ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች ብቻ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 224 04 62 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአገው ግምጃ ቤት ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

