ለመጀመሪያና ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
36

በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 15 በሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ. ሎት 1. አሮጌ ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ሎት 2. ጤፍ ሰብል ሸያጭ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ሎት 3. ሩዝ ሰብል ሽያጭ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ሎት 4. ዳጉሳ ሰበል ሽያጭ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ሎት 5. የቤት ማሰዋቢያ ዕቃዎች ግዥ ለሁለተኛ ጊዜ፣  ሎት 8.  የመጋዝን የወለል ጥገና የአገልግሎት ግዥ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ካላቸው አወዳድሮ የሚገዙትን መግዛትና የሚሽጡትን መሸጥ ይፈለጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅት መሳትፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
  2. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራቲ (ዋስትና) ወይም ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅርቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. ግልጽ ጨረታው በብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዳይሰበስብባቸዉ ፈቃድ የተሰጣቸዉ (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥዉ የሚሳተፍ ማንኛዉም ተጫራች ተጨማሪ እስት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና ሲፒኦ ሲያሲይዙ ቫት የሚጠይቁትን ጨምሮ መሙላትና ማሰያዝ አለባቸው፡፡ የሚጠይቀዉ የአንድ ወይም በጥቅል (ሎት) የሚገዛዉ እቃ እንጅ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም እና ፊርማ በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ዉስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 350 (ሶስት መቶ ሀምሳ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለወጣው ለ10 (አስር) ተከታታይ  የሥራ  ቀናት ለሁለተኛ እና ለሶሰተኛ ጊዜ ለወጣው ለ7 (ለሰባት)  ተከታታይ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 106 መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለወጣው ለ10 (አስር)  ተከታታይ የሥራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒዩኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ለሁለተኛ  ጊዜ ለወጣው ለ7 ተከታታይ  ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 7ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒዩኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ7ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  8. ቅዳሜ ለዩኒየኑ የሥራ ቀን ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. ጨረታው ተወዳዳሪዎች (ተወካዮቻቸው) በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
  10. የጨረታ አሽናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምሰት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አሽናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
  11. የሚፈልጉትን ሎት መርጦ መሙላት የሚቻል ሲሆን የንግድ ፈቃድ የማይጋብዝ ካልሆነ በስተቀር ለይቶ ወይም ቀንሶ (መርጦ) መሙላት አይቻልም፡፡
  12. በሎት ላይ የተጠቀሱት አሮጌ ያገለገሉ ዕቃዎች ውስጥ ከሎት 1.ሀ እሰከ ሎት ሐ ድረስ በሶስት ደረጃ የተመደበ ሰለሆነ ከሎት 1ሀ እስከ ሎት 1ሐ ድረስ የፈለጉትን መርጦ መሙላት ይችላሉ፡፡
  13. አሸናፊው ያሸነፈዉን እቃ በእራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ሊወስድ እና ሊያቀርብ ነዉ፡፡ የሚሽጡ ማንኛዉም እቃዎች መጠንና (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፡፡ አሸናፊዉ ከሎት ውጭ ያሉት የሚለየዉ በተናጠል ይሆናል፡፡
  14. አሸናፊዉ ያሸነፈበትን ግዥዎች (ሽያጭ) በፍትህ ዉሉ ከተመረመረ (ከተመዘገበ) የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊዉ ይከፍላል፡፡ ሰብሉን ለማንሳት የሚያሰፈለጉ ማንኛውም የወዛደር ማስጫኛ እና የትራንሰፓርት ወጭዎች አሽናፊ የሚሽፍን ይሆናል፡፡
  15. ሰብሉ የሚገኝበት ቦታ ባ/ዳር ከተማ ከዩኒየኑ መጋዘን የሚገኝ ሲሆን ጥራቱን በአካል በማየት መሙላት ይችላሉ፡፡
  16. በዚህ ያልተጠቀሱ ሃሳቦች ቢኖሩ በህ/ስ/ማህበራት የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
  17. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 09 11 59 05 34 /05 83 20 16 70 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላልሉ፡

መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተወሰነ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here