በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የኪንፋዝ በገላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ/ም በመደበኛ በጀት ማስፈፀሚያ ሎት 1. የተሸከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 2. የመኪና ጎማ፣ ሎት 3. የጭነት አገልግሎት፣ ሎት 4. የመኪና ቅባትና የዘይት አይነቶች እና ሎት 5. የተሸከርካሪ አሮጌ እቃዎች በግልጽ ጨረታ የግዥ ተጫራቾችን አወዳድሮ ዉል በመያዝ ማሰራት እና መግዛት እንዲሁም ሎት አምስትን ሽያጭ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋያነት መለያ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ለሎት 1. እና ለሎት 3. በበጀት አመቱ እስከ ሰኔ 30/2019 ዓ/ም ዉል በመያዝ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ፡፡
- ከተራ ቁጥር 1-4 የተዘረዘሩት የማወዳደሪያ መስፈርቶች ለሎት 5. የማያስፈልጉ በመሆናቸዉ ማንኛዉን ግለሰብ መወዳደር ይሚችላል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ክፍያ ማዘዣ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከመስሪያ ቤቱ ደረሰኝ በመቁረጥ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
- ከዚህ በላይ የተቀመጡትን የመወዳደሪያ መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት ክፍት ሲሆን በጎንደር ከተማ አባ ጃሌ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ህንፃ ቢሮ ቁጥር 14 ላይ ከዋና ገንዘብ ያዥ ብር 400 (አራት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መዉሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸዉን መ/ቤቱ ባዘጋጀዉ የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ዉስጥ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ብሎ በመለየት በአንድ በታሸገ ኢንቨሎፕ ፖስታ ዘወትር በስራ ስዓት ጠዋቱ ከ2፡30 እስከ 6፡30 እንዲሁም ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 11፡30 ድረስ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ የሚለየዉ በእያንዳንዱ በወጣዉ ሎት በጥቅል ዋጋ ይሆናል፡፡
- አሸናፊ የሚሆነዉ ድርጅት የዉል ማስከበሪያ (ሲፒኦ) ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ክፍያ ማዘዣ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከመ/ቤቱ ደረሰኝ በመቁረጥ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- አሸናፊ የሚሆነዉ ድርጅት ዉል የሚወስደዉ በጎንደር ከተማ አባ ጃሌ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ህንፃ ቢሮ ቁጥር 14 ላይ ይሆናል፡፡
- የእቃ እርክክብ ቦታ በጎንደር ከተማ አባ ጃሌ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ይሆናል፡፡
- ጨረታዉ በአስራ ስድስተኛዉ ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ጨረታዉ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በተዘጋጀዉ ዝርዝር መግለጫ መሰረት መሞላት ያለበት ሲሆን ከነጠላ ዋጋዉም ሆነ ከጠቅላላ ዋጋዉ ሥርዝ ድልዝ መሆን የለበትም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚመታዉ ማህተም ከንግድ ሥራ ፈቃዱ ጋር በቀጥታ ተዛማጅ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ስለ ጨረታዉ ዝርዝር ማብራሪያ ከፈለጉ በጎንደር ከተማ አባ ጃሌ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ህንፃ ቢሮ ቁጥር 14 ላይ በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 09 00 41 59 24 በመደወል መረጃ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የኪንፋዝ በገላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

