ኄር የበጎ አድራጎት ማህበር በሚል ስያሜ በበጎ አድራጎት ድርጅት እንዲመዘገብ እና ማህበሩ የሚጠቀምበት ከታች የተቀመጠው አርማ (ሎጎ) ህጋዊ እውቅና እንዲሰጥላቸው 01/01/2019 በተፃፈ ማመልከቻ ጠይቀዋል፡፡ ስለሆነም የድርጅቱን ስያሜ እና አርማ (ሎጎ) መመዝገብ የሚቃወም ካለ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አሰር) ተከታታይ የሥራ ቀናት መቃወሚያውን ይዞ አማራ ክልል ፍትህ ቢሮ የሰነዶች ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና የጠበቆች ጉዳይ ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 03 እንዲቀርቡ እያሳወቅን አስከተጠቀሰው ቀን ድረስ ካልቀረቡ የቀረበውን ስያሜና አርማ (ሎጎ) የምንመዘግብ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
አብክመ ፍትህ ቢሮ

