ውዝግብ ያስነሳው ተጫዋች

0
50

የኳታር ብሔራዊ የመረብ ኳስ ቡድን አባል ሆኖ ከሦስት አገራት ጋር በእስያ ሻምፒዮን ውድድር ተካፍሎ 40 ነጥብ ያስመዘገበው የ13 ዓመቱ ታዳጊ እድሜ አናሳነት እና ብቃት ከፍተኛነት ውዝግብ ማስነሳቱን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ ሰሞኑን አስነብቧል፡፡

ታዳጊው ሙባረክ ሙሳ ማዱት በእስያ አገራት የቮሊቦል ሻምፒዮና አገሩ ከታይላንድ ፣ቴይፒ እና ደቡብ ኮሪያ ጋር በገጠመችባቸው ጨዋታዎች 40 ነጥብ አስመዝግቧል፤ ቡድኑ በሦስቱም ጨዋታዎች ተሸናፊ ቢሆንም ፡፡

ሙባረክ 13 ዓመቱ ቢሆንም ቁመቱ 2 ሜትር ከ10 ሴንቲ ሜትር ነው፡፡ በዚህም ከቡድን አባላቱ ረጅሙ መሆን ችሏል፡፡ ከዚህ ባሻገር በመረብ ኳስ ጨዋታው ያሳያው ብቃት ብዙዎችን አስደምሟል፡፡

የተጫዋቹን የግል መረጃ የያዘው ድረ ገጹ ታዳጊው  በኅዳር 24/2012 እ.ኤ.አ በደቡብ ሱዳን መወለዱን እና ከጥቂት ዓመታት በኋላ የኳታር ዜግነት ማግኘቱን አስፍሯል፡፡ ይህ በመሆኑ አገሪቱን ወክሎ መሰለፍ ይችላል የሚሉም አስተያየታቸውን አስፍረዋል፡፡

አብዛኛዎቹ ጉዳዩን የተመለከቱ ባለሙያዎች ዕድሜውን ብቻ ሳይሆን በሜዳ ውስጥ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች በጣም በዕድሜ የበሰለ፣በስልጠና የተካነ ከመምሰሉ አንፃር አጣቅሰው ሞግተዋል፡፡እንደ አብነት ሲጠቅሱ የቡድን አባላቱ ከሚያደርጉት እቅስቃሴ በእጅጉ ከሁሉም የተሻለ መሆኑ ጥርጣሬ ውስጥ አስገብቷቸዋል፡፡

በመጨረሻም የሙባረክ ዕድሜ በግምት የተሰጠ እንዳይሆን በመስጋት መጣራት እንዳለበት ፣የአገሪቱ የመረብ ኳስ ፌድሬሽንም መልስ ሊሰጥበት እንደሚገባ ባለሙያዎቹ ስለመጠየቃቸው በመጠቆም ነው ጽሑፉ ያደማደመው፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የመስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ዕትም

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here