በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በወልድያ ከተማ ሪጅኦ ፖሊታንት የወልድያ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የግዥ ፋይ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት በ2019 በጀት ዓመት ለወልድያ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለአገልግሎት የሚውሉ ግብአቶችን ማለትም ሎት1. የንፅህና መጠበቂያ ፣ ሎት 2. ኤሌክትሮኒክስ እቃ፤ ሎት 3. መኪና ዘይትና (ቅባት) ሎት 4. የመኪና መለዋወጫ ፤ ሎት 5. የፅህፈት መሳሪያ ሎት ሎት 6. ቧንቧና መገጣጠሚያ፤ ሎት 7. የኬሚካል ግብአቶች እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡
- ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላችሁ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)ያላችሁ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆናችሁ፡፡
- ንግድ ፈቃድና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
- ከጨረታ ሰነዱና ከታሸገው ፖስታ ላይ የድርጀቱ ማህተም ተነባቢ በሆነ መልኩ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ጥራት ያላቸውን እቃዎች ማቅረብ አለባቸው፤ በቀረቡት እቃዎች ላይ ችግር ቢፈጠር የመመለስ (የመቀየር) ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ በህግ ፊት ይጠየቃሉ፡፡
- ተጫራቾች የአሸነፋበት የእቃ ዋጋ ድምር ብር ከ20,000 (ሃያ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ 3 በመቶ ተቀንሶ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት በጨረታ ሰነዱ ከተዘረዘሩት እቃዎች እስከ 25 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
- ተጫራቾች የሞሉት እቃ ድምር ዋጋ 2 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ቢን ቦንድ በኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ባንክ በተመሰከረለት ሲፒ ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ጥሬ ገንዘብ በእጅ ይዘው መቅረብ አይፈቀድም፡፡
- የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር (ሎት) ነው፡፡
- ጨረታውን አሸናፊው ድርጅት ከአሸነፈ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራስን ማግለል አይቻልም፡፡
- የሚገዙት እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለአማራ ክልል ከተሞች የመጠጥ ውሃና ፍሣሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የግዥ እና የንብረት አስተዳደር መመሪያ ተገዥ መሆን ይገባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸገው በ16ኛው የሥራ ቀን ከጥዋቱ 2፡30 ታሽጎ በዚሁ ቀን 3፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡የመክፈቻው ቀን በአል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ድርጅቱ ሳምፕል ስላስቀመጠ ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፏቸውን እቃዎች ወልድያ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች በተዘረዘረው የመሸጫ ዋጋ መሰረት ቢሮ ቁጥር 02 በመምጣት መግዛት ትችላላችሁ፡፡ ሎት1. የንፅህና መጠበቂያ ብር 300 ፣ ሎት 2. ኤሌክትሮኒክስ እቃ ብር 200 ፤ ሎት 3. መኪና ዘይትና (ቅባት) ብር 200 ሎት 4. የመኪና መለዋወጫ ብር 300፤ ሎት 5. የፅህፈት መሳሪያ ሎት ብር 300 ሎት 6. ቧንቧና መገጣጠሚያ፤ ብር 400 ሎት 7. የኬሚካል ግብአቶች ብር 200
- የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በውሃ አገልግሎቱ ድርጅት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 431 12 23 በመደወል ማግኘት ይችላል፡፡
የወልድያ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

