ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
13

የቢቡኝ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት አመት ሎት 1. የእንስሳት መድሀኒት፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሰለዚህ ለመጫረት የሚፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. በአዲሱ አዋጅ መሠረት የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ የሙያ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥ መጠኑ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ለየብቻዉ በማሸግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የግዥ ፈፃሚ መስሪያ ቤትና የተጫራቹን ሙሉ ስምና አድራሻ ፊርማና ማህተም በማስቀመጥ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ የጨረታ አሸናፊዉ የዉል ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
  6. የሚቀርቡት የእንስሳት የመድሃኒት ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) የማይመለስ ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር 20,000 (ሀያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሃሳባቸዉን ዋናውንና ቅጁን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቢቡኝ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥ/ን/አ ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በተዘጋጀው የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰኔ 1/2018 ዓ/ም እስከ ሰኔ 15/2018 ዓ/ም 11፡30 ድረስ መግዛት እና ማስገባት ይችላሉ፡፡
  10. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሉቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በግዥ /ንአስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 ለዕቃ አቅርቦት በ16ኛዉ ቀን  ሰኔ 16/2018 ዓ.ም 3፡00 ይታሸጋል፡፡ በዚሁ ቀን 3፡30 ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን መ/ቤቱ 20 በመቶ የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  12. መ/ቤቱ ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀን ብሄራዊ የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቀን ይከፈታል፡፡
  13. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በአካል በመገኘት መረዳት ይችላሉ፡፡

የቢቡኝ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here