ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
6

በማእከላዊ ጎንደር ዞን የምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አማካኝነት ለምሥራቅ ደንቢያ ወረዳ አስተዳደር ቢሮ ግንባታ 3ተኛ ዙር የጣራ፣ ዲች እና ሴፊቲ ታንከር ሥራዎች የእጅ ዋጋ  ግንባታ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች  የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸውና ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የጨረታ ሰነዱን ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከደረጃ ስድስት እና ከዚያ በላይ የሆኑ፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱን ከሰኔ 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ በምሥራቅ ደንቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. የግንባታ ዝርዘር መገለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 ከሰኔ 15/2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 05/2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩት ጠቅላላዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረስኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በታሸገ  ፖስታ በምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በ22 ቀን ሐምሌ 06/2018 ዓ.ም በ3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጣራ ስራና ሌሎች ሥራዎችን ሐምሌ 6/2018 ዓ.ም  በ22ኛው ቀን 3፡30 ተዘግቶ በምሥራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 በዚሁ ቀን በ4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
  12. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ለጨረታው መሟላት የሚገባቸው ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች በሌሉበት ጽ/ቤቱ የጨረታውን ፖስታ የመክፈት ስልጣን አለው፡፡
  13. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ተጫራቹ (ተወዳዳሪው) አሸናፊነቱ ተገልፆለት ውል ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ ያሸነፊውን 3ኛ ዙር የጣራ ስራና ሌሎች ሥራዎችን ሥራ መጀመር ይኖርበታል፡፡
  15. ተጫራቹ የሞላው ጠቅላላ ዋጋ ከማሀንዲስ ግምቱ 10 በመቶ በላይ ከሆነ እና ከ25 በመቶ  በታች ከሆነ ውድቅ ይደረጋል፡፡
  16. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 335 06 01 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- ከዚህ በፊት በየትኛዉም ደረጃ በነበራቸዉ የአፈጻጸም ችግር ምክንያት የታገዱ ተጫራቾችን አይመለከትም፡፡

የምስራቅ ደንቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here