የጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለጎንጅ ቆለላ ሴ/መቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት 1. የስፖርት እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ድረጅቱ ህጋዊ ማህተም ያለው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የዕቃውን አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፍል የጨረታ ሰነዱን ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጠር 6 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የግዥው ጠቅላላ ዋጋ 1/4ኛውን በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከነሐሴ 11/2018 እስከ ነሐሴ 26/2018 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ነሐሴ 26/2018 ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም ከረፋዱ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ መሞላት አለበት፡፡ ሆኖም ሥርዝ ድልዝ ካለ ስለመስተካከሉ ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ 20 በመቶ የመጨመር ወይም መቀነስ ይችላል እና ተጫራቾች ግዥ/ንብ/አስተ/ ቡድን ሳምፕል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት በጠቅላላው ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ሲሆን ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ሲያቀርብ ነው፡፡
- ከዚህ በላይ ያልተጠቀሱ የጨረታ መመሪያዎች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስተ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 556 75 58 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

