ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
43

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በወልድያ ከተማ ሪጅኦ ፖሊታንት የወልድያ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የግዥ ፋይ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት በ2019 በጀት ዓመት ለወልድያ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለአገልግሎት የሚውሉ       ግብአቶችን ማለትም   ሎት1. የንፅህና መጠበቂያ ፣ ሎት 2. ኤሌክትሮኒክስ እቃ፤ ሎት 3. መኪና ዘይትና (ቅባት) ሎት 4.  የመኪና መለዋወጫ ፤ ሎት 5.  የፅህፈት መሳሪያ ሎት   ሎት 6.    ቧንቧና መገጣጠሚያ፤  ሎት 7. የኬሚካል ግብአቶች  እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት  ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡

  1. ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላችሁ፡፡
  1. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)ያላችሁ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ፡፡
  3. የቫት ተመዝጋቢ የሆናችሁ፡፡
  4. ንግድ ፈቃድና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱ ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
  1. ከጨረታ ሰነዱና ከታሸገው ፖስታ ላይ የድርጀቱ ማህተም ተነባቢ በሆነ መልኩ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡
  2. ተጫራቾች ጥራት ያላቸውን እቃዎች ማቅረብ አለባቸው፤ በቀረቡት እቃዎች ላይ ችግር ቢፈጠር የመመለስ (የመቀየር) ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ በህግ ፊት ይጠየቃሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የአሸነፋበት የእቃ ዋጋ ድምር ብር ከ20,000 (ሃያ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ 3 በመቶ ተቀንሶ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  4. ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት በጨረታ ሰነዱ ከተዘረዘሩት እቃዎች እስከ 25 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
  5. ተጫራቾች የሞሉት እቃ ድምር ዋጋ 2 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ቢን ቦንድ በኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ባንክ በተመሰከረለት ሲፒ ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ጥሬ ገንዘብ በእጅ ይዘው መቅረብ አይፈቀድም፡፡
  6. የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር (ሎት) ነው፡፡
  7. ጨረታውን አሸናፊው ድርጅት ከአሸነፈ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራስን ማግለል አይቻልም፡፡
  8. የሚገዙት እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች ለአማራ ክልል ከተሞች የመጠጥ ውሃና ፍሣሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የግዥ እና የንብረት አስተዳደር መመሪያ                ተገዥ መሆን ይገባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  11. የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸገው በ16ኛው የሥራ ቀን ከጥዋቱ 2፡30 ታሽጎ በዚሁ ቀን 3፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡የመክፈቻው ቀን በአል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  12. ሳምፕል ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ድርጅቱ ሳምፕል ስላስቀመጠ ማየት ይችላሉ፡፡
  13. ተጫራቾች ያሸነፏቸውን እቃዎች ወልድያ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ድረስ በማምጣት ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
  14. የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች በተዘረዘረው የመሸጫ ዋጋ መሰረት ቢሮ ቁጥር 02 በመምጣት መግዛት ትችላላችሁ፡፡ ሎት1. የንፅህና መጠበቂያ ብር 300 ፣ ሎት 2. ኤሌክትሮኒክስ እቃ ብር 200 ፤ ሎት 3. መኪና ዘይትና (ቅባት) ብር 200 ሎት 4.  የመኪና መለዋወጫ ብር 300፤  ሎት 5.  የፅህፈት መሳሪያ ሎት ብር 300  ሎት 6.  ቧንቧና መገጣጠሚያ፤ ብር 400   ሎት 7. የኬሚካል ግብአቶች ብር 200
  15. የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በውሃ አገልግሎቱ ድርጅት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 431 12 23 በመደወል ማግኘት ይችላል፡፡

የወልድያ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here